የቀድሞው ተጫዋች ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነው

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ ክለቦች በመጫወት የሚታወቀው ተስፋሁን ጋዲሳ (ኮል) ከዓመታት ውስብስብ ችግር በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ትውልድ ሀገሩ ይመለሳል።

አመለሸጋ እንደሆነ የሚነገርለት እና ብዙዎች በቅፅል ስሙ “ኮል” ይበልጥ የሚያውቁት ተስፋሁን ጋዲሳ በኢትዮጵያ ቡና ጨምሮ በተለያዩ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች እና ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በየመን ሊግ በመጫወት ከፍተኛ ዝና እና ተወዳጅነት እንዳተረፈ ይታወቃል። ከባለቤቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር በርዕስ በዕርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኘው ተስፋሁን ወደ ትውልድ ሀገሩ ለመመለስ የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ምክንያት ወደ ሀገሩ ለመመለስ መቸገሩን ተከትሎ የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥያቄ ቀርቦ እንደነበረም ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገሩ የሚመጣበት ቅድመ ሁኔታዎች የተጠናቀቁ ሲሆን የፊታችን ሐሙስ ከነቤተሰቦች እንደሚመጣ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ