የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ቀጣይ ማረፊያ … ?

የሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮኑ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በቀጣይ የሚረከቡት ቡድን በቅርቡ ይታወቃል።

በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ክለብ አልባ የሆኑት እና ከዚህ ቀደም ከጅማ አባ ጅፋር እና ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት ባለታሪክ የሆኑት ስኬታማው አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ የሚገኙ ሲሆን ስማቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ጋር በተደጋጋሚ ቢነሳም አሰልጣኙን ለማሰናበት የወሰነው ሲዳማ ቡና የገብረመድኅን ግልጋሎትን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው እና ከአንድ የክለቡ የቦርድ አባል ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ሰምተናል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ከስምምነት እንደደረሱና ከሰሞኑ የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር የአሰልጣኙ ቀጣይ ማረፊያ ሲዳማ ቡና ሊሆን እንደሚችልም ከምንጮቻችን ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ