ወላይታ ድቻ የአምበሉን ውል አራዘመ

በርካታ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሰው ወላይታ ድቻ የአምበሉ ደጉ ደበበን ውል አራዝሟል።

በአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ደጉ በቅዱስ ጊዮርጊስ አስራ አራት የተሳዉ ዓመታትን አሳልፎ ከተለያየ በኋላ በ2011 አጋማሽ ወላይታ ድቻን መቀላቀሉ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት ዓመታትም በወጥነት ግልጋሎት የሰጠው ደጉ በዚህ ወር ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ከክለቡ ጋር ባደረገው ውይይት ከስምምነት በመድረስ ለተጨማሪ ዓመት በወላይታ ድቻ መለያ የሚያቆየውን ውል ለማራዘም ተስማምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ