ሀዲያ ሆሳዕና የቡድን መሪውን አግዷል

ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮቹ ዙሪያ ስብስባ የተቀመጠው ሀዲያ ሆሳዕና የቡድን መሪውን ያገደበትን ውሳኔ አሳልፏል።

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መልካም ጅማሮ አድርጎ አራት ተከታታይ ድሎችን አስመዝግቦ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና በቀጣይ ጨዋታዎች ውጤቱን ማስቀጠል ሳይችል ቆይቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ክለቡ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን የተመለከተ ግምገማ ያደረገበትን ስብሰባ ትናንት አከናውኗል፡፡

ስብሰባውን ተከትሎም ዛሬ በሥራ አስኪያጁ አቶ መላኩ ማደሮ አማካይነት በተፃፈ ደብዳቤ የቡድን መሪው የነበሩት አቶ መልካሙ ፀጋዬን ማገዱን ገልጿል። ለቡድን መሪው መታገድ ክለቡ ያስቀመጠው ምክንያትም ቡድን መሪው በውድድር ወቅት ተግባርና ኃፊነታቸውን ባለመወጣታቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ