ጅማ አባ ጅፋር የዕግድ ውሳኔ ተላለፈበት

አስቀድሞ የተስማሙበትን ስምምነት ተግባራዊ አላደረገም በሚል ፌዴሬሽኑ ጅማ አባ ጅፋር ላይ የዕግድ ውሳኔ አስተላለፈ።

ባሳለፍነው ዓመት ቡድኑን እያገለገሉ የነበሩ በርከት ያሉ ተጫዋቾች የሙሉ ክፍያ እና የወራት ክፍያ አልተፈፀመልንም በማለት ክስ መመስረታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት ጅማ አባ ጅፋር ለተጫዋቾቹ ክፍያውን እስኪፈፅም ድረስ ፌዴሬሽኑ ማንኛውም አገልግሎት እንዳያገኝ ዓምና ዕግድ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ሆኖም ክለቡ በተለያየ ጊዜ ደሞዛቸውን ለመክፈል ማሰቡን ባሸማጋዮች በኩል የመፍትሔ ሀሳብ በማቅረቡ ተጫዋቾቹ ይህን ሀሳብ ተቀብለው ቢስማሙም በተቀመጠው ቅድመ ስምምነት መሠረት እስካሁን ዕለት ደሞዛችን ሊከፈለን አልቻለም በማለት ለፌዴሬሽኑ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ፌዴሬሽኑ ጅማ አባ ጅፋር ውሳኔውን ተግባራዊ እስኪያደርግ ከማንኛውም አገልግሎቶች ያገደ መሆኑን በደብዳቤ አሳውቋል።© ሶከር ኢትዮጵያ