አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል ራሳቸውን ከኃላፊነት አንስተዋል

በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ የሚገኘውን አዳማ ከተማን ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ራሳቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን አሳውቀዋል።

ያለፉትን ሰባት ዓመታት አይቶት በማያውቀው የውጤት ማጣት እና የፋይናስ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው አዳማ ከተማ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከተለያየ በኋላ አስቻለው ኃይለሚካኤልን በዘንድሮ ዓመት ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ይታወቃል። ቡድኑ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን አሰልጣኝ አስቻለው ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ በሰጡት አስተያየትም በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በፊት ራሳቸውን ለማግለል ወስነው የነበረ ቢሆንም ከአመራሮች ጋር ተነጋግረው ለዚህ ጨዋታ እንደቀረቡ ከጨዋታው በፊት ለሱፐር ስፖርት በሰጡት አስያየት ላይ ጠቁመው ነበር።

በቀጣይ ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ይሾማል ወይስ በረዳቶቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ