እዮብ ዓለማየሁ ወደ ቡድኑ ሊመለስ ነው

በቅርቡ ከቡድኑ መቀነሱን ተከትሎ ቅሬታውን አሰምቶ የነበረው እዮብ ዓለማየሁ ወደ ቡድኑ እንዲመለስ ሊደረግ ነው።

የመስመር አጥቂው ከቀናት በፊት ከቡድኑ የተቀነሰበት ምክንያት አሳማኝ አለመሆኑን፣ ውል እያለው እንደተቀነሰ  እና የህክምና ክትትል ክለቡ እያደረገለት አለመሆኑን ጠቅሶ ቅሬታውን ለሶከር ኢትዮጵያ ማቅረቡ ይታወቃል። አሁን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ እዮብ ከቡድኑ አስቀድሞ የተቀነሰው የአቅም ችግር ኖሮበት ሳይሆን የጤናው ሁኔታ ለጨዋታ ዝግጁ የማያደርገው እንደሆነ እና ቡድኑ ከነበረበት የውጤት ስጋት አኳያ የማይጫወት ከሆነ ቡድኑን በሱ ቦታ ሰው በመተካት የተሻለ ውጤት ለማምጣት በማሰብ እንደሆነ የክለቡ አመራሮች ጠርተው በማናገር በኃላም በቡድን መሪው አማካኝነት መቀነሱ እንደተነገረው ገልፀዋል። አሁን ግን የህክምና (MRI) ምርመራ ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ መጫወት የሚያስችለው የጤና ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከነገ ጀምሮ ወደ ባህር ዳር በመሄድ ቡድኑን እንዲቀላቀል መወሰኑን ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ