ድሬዳዋ ከተማ አማካይ አስፈርሟል

ድሬዳዋ ከተማ በዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ፡፡

ሄኖክ ገምቴሳ ብርቱካናማዎቹን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። በአዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ እና ጅማ አባጅፋር ተጫውቶ ያሳለፈው ተጫዋቹ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ወደ ወልዋሎ ዓ/ዩ አምርቶ የነበረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተጫወተባቸው ክለቦች ያሰለጠኑት ዘማርያም ዘልደጊዮርጊስን ተከትሎ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የምስራቁን ክለብ ተቀላቅሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ