ሲዳማ ቡና ከ ባህር ዳር ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የ14ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎችን እነሆ !

ባህር ዳር ከተማ ከዕረፍቱ በፊት በነበረው የድቻው ጨዋታ ባደረጋቸው ሁለት ለውጦች ግርማ ዲሳሳ እና ባዬ ገዛኸኝ ወደ አሰላለፍ ሲመጡ ሳለአምላክ ተገኘ እና ምንይሉ ወንድሙ አርፈዋል።

ሲዳማ ቡና በተከላካይ ክፍሉ ላይ ባደረጋቸው ሦስት ለውጦች ቅጣት ላይ ባለው ፈቱዲን ጀማል ፣ አማኑኤል እንዳለ እና ግሩም አሰፋ ምትክ አዲስ ፈራሚዎቹ ሽመልስ ተገኝ እና መሀሪ መና እንዲሁም ሰንደይ ሙቱኩ ጨዋታውን ጀምረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጉዳት ላይ ያለው ዮሴፍ ዮሃንስ እና አዲሱ አቱላ በአዲስ ፈራሚው ዮናስ ገረመው እና ከጉዳት በተመነሰው ይገዙ ቦጋለ ተተክተዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ነባር እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማጣመር ለዛሬው ጨዋታ መቅረባቸውን ሲገልፁ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በበኩላቸው ሲዳማን በመጀመሪያው ዙር እንደረቱት ሁሉ ዛሬም በመድገም ደጋፊዎቻቸውን ለመካስ ማሰባቸውን ገልፀዋል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ፌደራል ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ ተመድበዋል።

የቡድኖቹ ቀዳሚ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
7 ሽመልስ ተገኝ
32 ሰንደይ ሙቱኩ
24 ጊት ጋትኮች
5 መሀሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
20 ዮናስ ገረመው
10 ዳዊት ተፈራ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
26 ይገዙ ቦጋለ

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪስተን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
7 ግርማ ዲሳሳ
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
9 ባዬ ገዛኸኝ


© ሶከር ኢትዮጵያ