ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአስራ አምስተኛ ሳምንት የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታን የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎች እንደሚከተለው አቅርበናል።

በባህር ዳር ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ እና በከተማው ያላቸውን ቆይታ በመልካም ለማገባደድ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ የገለፁት አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ ከድሬዳዋው ጨዋታ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ዳንኤል ኃይሉ እና ያሬድ ሀሰንን በአብዱልሀፊዝ ቶፊቅ እና ቃልኪዳን ተተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል።

አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት በበኩሉ ሊጉ ሲጀመር ቡድኑ የነበረበትን ክፍተት እያስተካከለ እንደመጣ እና በእረፍቱ የተጫዋቾቻቸውን የሥነ-ልቦና ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ሲሰሩ እንደነበር በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል። አሠልጣኙ በ13ኛ ሳምንት አራፊ ከነበረበት ጊዜ በፊት ድሬዳዋን ሲገጥም ከተጠቀመው የመጀመርያ 11 ሦስት ተጫዋቾችን ለውጧል። በዚህም ፀጋአብ ዮሐንስ፣ ጋብርኤል አህመድ እና ወንድምአገኝ ኃይሉ በዘነበ ከድር፣ አለልኝ አዘነ እና ዮሐንስ ሰጌቦ ተክተዋል።

ፌደራል ዳኛ ሐብታሙ መንግስቴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት አርቢትር ናቸው።

ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሀመድ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
16 ቃልኪዳን ዘላለም
7 ቡልቻ ሹራ
16 ፍፁም ገብረማርያም

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
2 ዘነበ ከድር
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
18 ዳዊት ታደሰ
23 አለልኝ አዘነ
19 ዮሐንስ ሰጌቦ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ