ሲዳማ ቡና የውጪ ዜጋ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ፋቢያን ፋርኖሌ በይፋ ሲዳማ ቡና ተቀላቅለ፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደካማ የውድድር ዓመትን እያሳለፈ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የአሰልጣኝ ለውጥ ካደረገ በኃላ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የቤኒን ዜግነት ያለው ፋቢያን ፋርኖሌን ሰባተኛ አዲስ ተጫዋች በማድረግ ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡

በፈረንሳይ የተወለደው እና በዛው ፈረንሳይ ለቦርዶ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ግብ ጠባቂ ያለፉት ዓመታት በቱርክ ሊግ ለየኒ ማልታይስፖር እና ኢዝሩምስፖር በመጫወት አሳልፏል፡፡ እስካሁን ለአስር ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ ግብ ጠባቂ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለሲዳማ ቡና ፊርማውን አኑሯል። ተጫዋቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ተሳታፊ የሆነው በቤኒን ብሔራዊ ቡድንን ለመቀላቀል ተጉዟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ