የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሁለት አመራሮቹ ላይ የእገዳ ውሳኔ አስተላለፈ

ፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ላይ ውክልና ሳይኖራቸው ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸው ሁለት አመራሮቹን ማገዱን ይፋ አድርጓል።

ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው መረጃ የሚከተለው ነው:-

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተላለፈ ውሳኔ
**************************************

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ መጋቢት 20/2013 ከቀኑ 10 ሰዓት በአቢጃ ኮትዲቯር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውክልና ሳይሰጣቸው በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ተገኝተው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመወከል ምርጫ የመረጡት የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ 13ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ድረስ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። በተጨማሪም ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን በምርጫው ተወዳዳሪ ሆነው እንዲሳተፉ ከኢእፌ እውቅና ውጪ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሳይወስን ማንንም ሳያማክሩ ደብዳቤ የጻፉት የኢእፌ ም/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ይህ ስብሰባ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ከስራ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ ተላልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ