አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ወልቂጤ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ያደረጓቸው ለውጦች እና መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል።

ወልቂጤዎች ከሀዋሳ አቻ ከተለያየው ስብስብ አሜ መሐመድ (ቅጣት)፣ አልሳሪ አልመሐዲ እና አህመድ ሁሴን አርፈው በምትካቸው ሄኖክ አየለ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ያሬድ ታደሰ የሚሰለፉ ይሆናል። “እኛ እያሰብን ያለነው የራሳችንን ስራ ነው። የዛሬው ጨዋታ ላይም ትኩረት አድርገናል። ዝግጁ ነን” ሲሉም አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ ተናግረዋል።

በሰበታ ከተማ በኩል አዳማን ከረቱበት አሰለለፍ የአራት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገው ዓለማየሁ ሙለታ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ መስዑድ መሐመድ እና ታደለ መንገሻን በማሳረፍ በምትካቸው ፍፁም ገብረማርያም፣ ጌቱ ኃይለማርያም፣ ቡልቻ ሹራ እና መሳይ ጳውሎስ ተካተዋል። “የዛሬው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን አምናለሁ። ካቀድነው በላይ ቤስት አምስት ውስጥ ለመግባት የወልቂጤን ጨዋታ ለማሸነፍ ነው ወደ ሜ የምንገባው።” ሲሉ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ተናግረዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው በመሐል ዳኝነት ይመራዋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህን ይመስላል:-

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
23 ዮናታን ፍስሐ
30 ቶማስ ስምረቱ
4 መሐመድ ሻፊ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
25 ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
8 አቡበከር ሳኒ
20 ያሬድ ታደሰ
26 ሄኖክ አየለ

ሰበታ ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
5 ጌቱ ኃይለማርያም
13 መሳይ ጳውሎስ
12 ቢያድግልኝ ኤልያስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
8 ፉአድ ፈረጃ
28 ክሪዚስቶም ንታምቢ
16 ፍፁም ገብረማርያም
7 ቡልቻ ሹራ
77 ኦሰይ ማውሊ