አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሲዳማ ቡና ከ ጅማ አባ ጅፋር

የ25ኛው ሳምንት ሦስተኛ ቀን የረፋድ ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የአሰልጣኞች አስተያየት ይህንን ይመስላል።

ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና አቻ ከተለያየው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጎ በሀብታሙ ገዛኸኝ፣ ፋቢያን ፋርኖሌ እና ፈቱዲን ጀማል ምትክ ፍቅሩ ወዴሳ፣ ግርማ በቀለ እና ቢንያም በላይን ይጠቀማል። ” ለነገ ቀጠሮ የምንይዝበት ነገር የለም። በዚህ ጨዋታ ላይ ለመጨረስ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው” ሲሉም አሰልጣኝ ገብረመድኅን ተናግረዋል።

በጅማ አባ ጅፋር በኩል ከባህር ዳር ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጎ ዋውንጎ ፕሪንስ፣ ራሂም ኦስማኖ እና ሥዩም ተስፋዬ ምትክ ሳዲቅ ሴቾ፣ ኤልያስ አታሮ እና ወንድማገኝ ማርቆስ ተካተዋል። ፋሲል ከነማን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት አሰልጣኝ ፀጋዬ 12ኛ ደረጃን ይዞ ለመጨረስ ውጤቱን እንደሚፈልጉት ተናግረዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሀን ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ሲዳማ ቡና

1 ፍቅሩ ወዴሳ
3 አማኑኤል እንዳለ
19 ግርማ በቀለ
32 ሰንደይ ሙቱኩ
5 መሐሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
29 ያሳር ሙገርዋ
4 ቢንያም በላይ
8 ኢኪኪ አፎላቢ
27 ማማዱ ሲዲቤ

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
2 ወንድማገኝ ማርቅስ
4 ከድር ኸይረዲን
16 መላኩ ወልዴ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
24 ዋለልኝ ገብሬ
20 ሀብታሙ ንጉሤ
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ