ቡናማዎቹ የአማካያቸውን ውል አድሰዋል

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የአማካያቸውን ውል አራዝመዋል።

እስካሁን የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር የፈፀሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከደቂቃዎች በፊት የአማካይ መስመር ተጫዋቻቸው ሬድዋን ናስርን ውል ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራዝመዋል። በተሰረዘው የውድድር ዓመት አዲስ አበባ ከተማን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው ሬድዋን በተከላካይ አማካይ ሚና ቡናማዎቹን በጥሩ ብቃት ሲያገለግል ቆይቷል። አሠልጣኝ ካሳዬ አራጌም የተጫዋቹም ግልጋሎት ለተጨማሪ ዓመት ፈልገው እስከ 2016 ድረስ አስፈርመውታል።