ሰበታ ከተማ የተከላካዩን ውል አራዝሟል

አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠረ በኃላ ወደ ዝውውሩ በመግባት ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ሰበታ ከተማ አሁን የተከላካዩን ውል አራዝሟል።

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለመመራት በቅርብ ይፋ ያደረጉት ሰበታዎች ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ ቡድኑን ፕሪሚየር ሊግ እስከገባበት ጊዜ አንስቶ አሁንም ድረስ እያገለገለ የሚገኘው ጌቱ ኃይለማርያምን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል፡፡

ሰበታ ከተማ ከከፍተኛ ሊግ ሲያድግ በአምበልነት ቡድኑን የመራው ተከላካዩ በቀኝ መስመር ተከላካይነት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በሰበታ መለያ የምንመለከተው ይሆናል፡፡