ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ መስመር ተጫዋችን በሦስት ዓመት ውል አስፈረመ፡፡

አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ዕለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ነስረዲን ኃይሉን በሦስት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ የቀድሞ የለገጣፎ እና መከላከያ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመከላከያ ውል እያለው ከተለያየ በኋላ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቶ ጥሩ የውድድር ዓመትን ካሳለፈ በኃላ ማረፊያው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል፡፡