ጅማ አባጅፋር ፈጣኑን የመስመር አጥቂ አስፈረመ

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ከገባ በኃላ ሦስት አዳዲስ ፈራሚዎችን በእጁ ያስገባው ጅማ አባጅፋር የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

የመስመር ተጫዋቹ እዮብ ዓለማየሁ በሁለት ዓመት ውል ጅማን የተቀላቀለው ተጫዋች ሆኗል። በወላይታ ድቻ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥ አንፀባራቂ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን በማድረጉ በ2008 ወደ ዋናው ካደገ በኋላ ጥሩ ጊዜያትን ማሳለፍ የቻለው ወጣቱ ተጫዋች ሰባት ዓመታት ያሳለፈበት ወላይታ ድቻን በመልቀቅ ወደ ጅማ አምርቷል፡፡

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጫዋቹን ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ ማሰልጠናቸውም ይታወሳል፡፡