ዱላ ሙላቱ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቷል

ፈጣኑ የመስመር እና የፊት አጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዱላ ሙላቱ የጅማ አባጅፋር አምስተኛ ፈራሚ ሆኗል፡፡

በዝውውሩ ላይ በዛሬው ዕለት ገብተው በትጋት እየተሳተፉ የሚገኙት ጅማ አባጅፋሮች ፈጣኑን የመሰመር እና የፊት አጥቂ ዱላ ሙላቱን በሁለት ዓመት የውል ኮንትራት አስፈርመዋል፡፡ የቀድሞው ነቀምት ከተማ፣ ደቡብ ፖሊስ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና አዳማ ከተማ ተጫዋች ዱላ ወደ ቀድሞው ክለቡ ሀድያ ሆሳዕና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከተመለሰ በኃላ በክለቡ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በሀድያ ሆሳዕና ሊያራዝም ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም በአዳማ እና በሀድያ ሆሳዕና ያሰለጠኑት አሸናፊ በቀለን ጥሪ ተቀብሎ አባጅፋሮችን መቀላቀሉ ዕርግጥ ሆኗል፡፡