አማካዩ አዲስ ህንፃ ስድስተኛ የወላይታ ድቻ አዲስ ፈራሚ በመሆን ሶዶ ደርሷል፡፡
በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም መሪነት አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘውን ወላይታ ድቻ አማካዩ አዲስ ህንፃን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ የቀድሞው የመድን፣ ባንክ፣ ደደቢት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ወደ ሱዳኑ አልሀሊ ሸንዲ ተጉዞ ሦስት ዓመታትን ካሳለፈ በኃላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለአዳማ ከተማ መጫወቱ አይዘነጋም። የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ያሳለፈው አዲስ ህንፃ በአንድ ዓመት ውል ወደ ወላይታ ድቻ የክለቡ ስድስተኛ አዲስ ፈራሚ ሆኖ አምርቷል፡፡