የሳላዲን ሰዒድ ወቅታዊ ጉዳይ ?

በሳላዲን ሰዒድ ቀጣይ ሁኔታ አስመልክቶ የሚነሱ የተለያዩ ጉዳዮችን አስመልክቶ ይህን ዘገባ ለማጠናቀር ወደናል።

ከአዲሱ ሚሌኒየም ወዲህ በኢትዮጵያ እግርኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያቆየው ኮንትራት በዚህ ዓመት የሚጠናቀቅ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በፈረሰኞቹ ቤት ይቆያል አይቆይም የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ዜና ሆኖ ቆይቷል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ በክለቡ በኩል መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አዳጋች ሆኗል። ሆኖም ግን ባደረግነው ማጣራት ሳላዲን ሰዒድ እስከ ነሐሴ ሠላሳ ድረስ ኮንትራት እንዳለው እና በቅርቡ ለዓመታት ካገለገለበት ክለቡ ጋር እንደሚለያይ ከታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።

ሳላዲን ሰዒድ የክለብ እግርኳስ ህይወቱን በሙገር ሲሚንቶ ከጀመረ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኃላም ከኢትዮጵያ ውጭ ዋዲ ዴግላ፣ ሊርስ (ውሰት)፣ አል አህሊ ኤምሲ አልጀር ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተባቸው ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ከ2000-2002፣ ከ2008 ጀምሮ በአጠቃላይ ለስምንት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት በቆየበት ጊዜያት በርካታ ድሎችን ማጣጣሙ ይታወቃል።

በቀጣይ ሳላዲን ሰዒድ የተመለከቱ መረጃዎች የእርሱን ሀሳብ አካተንበት የምንመለስ መሆኑን እንጠቁማለን።