ጅማ አባጅፋር ወጣቱን ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ወጣቱ የግብ ዘብ ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል፡፡

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከቀጠረ በኃላ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን እያዘዋወረ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ግብ ጠባቂው ለይኩን ነጋሽን በአንድ አመት ውል ወደ ክለቡ ቀላቅሎታል፡፡ ከሲዳማ ቡና ከ17 ዓመት ቡድን 2009 ላይ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኃላ ያለፉትን አምስት አመታት በክለቡ ያሳለፈው ወጣቱ የግብ ዘብ ከሲዳማ ቡና ጋር ውሉ በመጠናቀቁ በቅርቡ አቡበከር ኑሪን ወደ ባህር ዳር ወደሸኘው ጅማ አባጅፋር አምርቷል፡፡