ጅማ አባጅፋር የሁለገብ ተጫዋቹን ውል አራዝሟል

በዛሬው ዕለት የሳላዲን ሰዒድን ዝውውር ያጠናቀቀው ጅማ አባ ጅፋር የነባር ተጫዋቹን ውል አራዝሟል።

በርከት ያሉ ዝውውሮችን እያጠናቀቀ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር አሁን ደግሞ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ለቡድኑ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሱራፌል ዐወልን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ከክለቡ ጋር የሚቆይበትን ውል አራዝሟል። ባለ ግራ እግሩ ተጫዋች ሱራፌል ዐወል ከዚህ ቀደም ለጅማ አባቡና፣ ሰበታ ከተማ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን በጅማ አባ ጅፋር ያለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታው በአማካይ እና የመስመር አጥቂነት ጨምሮ በተለያዩ ሚናዎች ሲያገለግል መቆየቱ ይታወሳል።