አዲሱ የሲዳማ ቡና ተጫዋች ለህፃናት ማሳደጊያ ተቋም ድጋፍ አድርጓል

በቅርቡ ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፍሬው ሰለሞን ለህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ፣ መከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ዘንድሮ ወልቂጤ ከተማን በመልቀቅ ወደ ሲዳማ ቡና መዘዋወር የቻለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፍሬው ሰለሞን በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ አቤንኤዘር ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ ተቋም በትናንትናው ዕለት በመገኘት ምግብ እና የምግብ እህል አበርክቷል፡፡

የሀዋሳ ትዝታ በተሰኘው የፌስቡክ ገፅ አባላት ጥሪ ቀርቦለት ድጋፉን የለገሰው ተጫዋቹ በቀጣዩቹ ቀናት ህፃናቱ ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ለመስጠት ቃል መግባቱን ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች፡፡