ዐፄዎቹ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ቀን ታውቋል

በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ፋሲል ከነማዎች ከ አል ሂላል ጋር የሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች የሚደረጉባቸው ቀናት ታውቀዋል።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆኑት ፋሲል ከነማዎች በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ ዝግጅታቸውን በባህር ዳር እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅቱን የቀጠለው ክለቡም በወጣለት ዕጣ መሰረት ከሱዳኑ የሊግ አሸናፊ አል ሂላል ጋር የሚያደርገው ጨዋታ መቼ እንደሆነ ሲጠባበቅ ነበር።

የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ ፋሲል ከነማ ከአል ሂላል ጋር መስከረም 2 የመጀመሪያ ጨዋታውን ባህር ዳር ላይ እንደሚያደርግ ያመላክታል። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ደግሞ ከሳምንት በኋላ መስከረም 9 ሱዳን ላይ እንደሚከናወን ተጠቁሟል።