የስፖርት ዞን የዓመቱ የዕውቅና ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል

ስፖርት ዞን የሬድዮ ፕሮግራም በስድስት ዘርፎች እና ታሪክ ለሰሩ ግለሰቦች ያዘጋጀው የዕዉቅና ፕሮግራም ነገ ምሽት ይካሄዳል።

በተለይ በሀገር ውስጥ እግርኳስ ትኩረቱን በማድረግ ያለፉትን ስድስት ዓመት በሬዲዮ ፕሮግራሙ የሚታወቀው “ስፖርት ዞን” ለወራት ሲቀሳቀስ የቆየበትን የዕውቅና አሰጣጥ መርሐግብር ነገ ምሽት ከአስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ሀያ ሁለት በሚገኘው ቼክ ኢን ሆቴል ያካሄዳል።

የተለያዩ እግርኳሱ እውቅ ሰዎች በክብር እንግድነት በሚታደሙበት በዚህ ፕሮግራም ላይ በእግርኳሱ በስድስት ዘርፍ የመጨረሻ ዕጩ ሆነው የቀረቡት ስፖርተኞች ሽልማታቸውን የሚያገኙ ሲሆን በእግርኳሱ የላቀ አስተዋፆኦ ያበረከቱ ግላቦች ልዩ የዕውቅና ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።

የመጨረሻ እጩዎች

ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ: ሚኬል ሳማኬ፣ ባህሩ ነጋሽ እና አቡበከር ኑሪ

ምርጥ ዋና ዳኛ ዘርፍ: ቴዎድሮስ ምትኩ፣ በላይ ታደሰ፣ ኤፍሬም ደበሌ

ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች ዘርፍ: አቡበከር ኑሪ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዊልያም ሰለሞን

ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ: ሥዩም ከበደ፣ ካሣዬ አራጌ፣ ዘላለም ሽፈራዉ

ተጓዥ ደጋፊ ዘርፍ: ፋሲል ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና

ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ: ያሬድ በየህ፣ አቡበከር ናስር፣ ሽመክት ጉግሳ