መከላከያ አጥቂ አስፈርሟል

በቢሾፍቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እየከወኑ የሚገኙት መከላከያዎች የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ መቀመጫውን በማድረግ ለ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ እና ረዳቶቹ እየተመራ እየሰራ የሚገኘው መከላከያ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ገዛኸኝ ባልጉዳን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

የቀድሞው የነቀምት ከተማ እና ሲዳማ ቡና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ገዛኸኝ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በከፍተኛ ሊጉ አዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን ከሌሎች የቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆንም ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ አሳድጓል፡፡ ከአዲስ አበባ ጋር ቀሪ የወር ዕድሜ ኮንትራት ያለው አጥቂው ማረፊያውን ሌላኛው አዳጊ ክለብ ለሆነው መከላከያን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ፈርሟል፡፡