አርባምንጭ ከተማ ሁለተኛ ኬንያዊ ተጫዋች አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ኬንያዊ አጥቂ በይፋ አስፈረመ፡፡

ከቀናት በፊት ኬንያዊው የመሐል ተከላካይ በርናንድ አቼንግን በይፋ ወደ ክለቡ መቀላቀል የቻለው አርባምንጭ ከተማ በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ኬንያዊ ፈራሚ በማድረግ አጥቂው ኤሪክ ካፓይቶን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል፡፡

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በባህርዳር ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ከተመለከቷቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ኤሪክ ከኬንያው የዲቪዚዮን ክለብ ሊጂ ንዶንጎ ከተገኘ በኋላ ኤፍሲ ታላንታ እና ከ2018 ጀምሮ ደግሞ በዛው ኬኒያ ካሪዮቫንጊ ሻርክስ በተባለ ቡድን ውስጥ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አርባምንጭ ከተማን ተቀላቅሏል፡