ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድርን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀው መከላከያ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል አድሷል።

ሴናፍ ዋቁማ ውላቸውን ካራዘሙት መካከል ናት። ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከተገኘች በኋላ በአዳማ ከተማ እንዲሁም የ2013 የውድድር ዘመንን በጦሩ ያሳለፈችው የግብ ቀበኛዋ ሴናፍ ዋቁማ ከንግድ ባንክ ዝውውር ጋር ስሟ ተያይዞ የነበረ ቢሆንም ባለመሳካቱ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ውሏን አራዝማለች፡፡

ሌላኛዋ ውል ያደሰችሁ ተጫዋች የቀድሞው የንግድ ባንክ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ደግሞ መከላከያን በአምበልነት እና በመሐል ተከላካይነት ስታገለግል የነበረችው ፅዮን እስጢፋኖስ በቀጣይም በክለቡ መቆየቷ ተረጋግጧል፡፡