ሊግ ካምፓኒው ነገ ከክለቦች ጋር ይወያያል

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ጅምሩን የሚያደርግ ሲሆን ነገ ካምፓኒው በ2014 የውድድር ደንብ ዙሪያ ይወያያል፡፡

የ2014 የውድድር ዘመን ቤትኪንግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በያዝነው ሳምንት ዕሁድ ጥቅምት 7 በሚደረጉ ሁለት መርሀግብሮች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጀመራል፡፡ ውድድሩ በርካታ ተመልካቾች እንዲመለከቱት በሚልም ከቀትር በኋላ እና ምሽት ላይ እንዲደደረግ የተወሰነ ሲሆን ዘጠኝ ሳምንታትን በሀዋሳ ክለቦች በውድድር ያሳልፋሉ፡፡

ውድድሩ ከመጀመሩ አስቀድሞ የሊጉ ተሳታፊ አስራ ስድስት ክለቦች ለ2014 በተዘጋጀው ደንብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ሼር ካምፓኒው እና ክለቦች ቀጠሮ ይዘዋል። ረቡዕ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮም በሊግ ካምፓኒው ፅህፈት ቤት አዳራሽ ይህ የደንብ ውይይት እንደሚደረግ ድረገፃችን ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡