አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ወልቂጤ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

የምሽቱ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎችን ተካፈሉ !

ዮናስ በርታ እና ረመዳን የሱፍን በጉዳት እና ቅጣት ያጡት ወልቂጤዎች በምትካቸው ውሀብ አዳምስ እና አበባው ቡታቆን አስገብተዋል። ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች ጫላ ተሺታ እና ያሬድ ታደሰም አህመድ ሁሴን እና እስራኤል እሸቱን በመተካት በአሰላለፍ ውስጥ ተካተዋል። በፋሲል ከነማ በኩል ደግሞ በዛብህ መለዮ በሳሙኤል ዮሀንስ ቦታ የጀመተበት ቅያሪ ከሀዲያ ሄሳዕናው ጨዋታ የተደረገ ብቸኛ ለውጥ ሆኗል።

አሰልጣኝ ዻውሎስ ጌታቸው ተጋጣሚያቸው ቻምፒዮን በመሆኑ ቢያከብሩትም ጨዋታውን ሳያከብዱ አጥቅተው ለመጫወት እንደሚገቡ ሲናገሩ የፋሲል አቻቸው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በበኩላቸው ከባለፈው ጨዋታ መጠነኛ የአጨዋወት ለውጥ እንደሚያደርጉ እና ለሁሉም ጨዋታ ትኩረት እንደሚሰጡ ሁሉ ዛሬም ተመሳሳዩን እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

ፌደራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

ወልቂጤ ከተማ

1 ሲልቪያን ህቦሆ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
19 ዳግም ንጉሴ
24 ውሀብ አዳምስ
4 አበባው ቡታቆ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
8 በኃይሉ ተሻገር
14 አብዱልከሪም ወርቁ
7 ጫላ ተሺታ
20 ያሬድ ታደሰ
9 ጌታነህ ከበደ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
13 ሰዒድ ሀሰን
16 ያሬድ ባየህ
15 አስቻለው ታመነ
5 ከድር ኩሊባሊ
17 በዛብህ መለዮ
14 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
19 ሽመክት ጉግሳ
7 በረከት ደስታ
9 ፍቃዱ ዓለሙ