የአንደኛ ሊግ ውድድር የዕጣ ማውጫ ቀን ታወቀ

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት እና የደንብ ውይይት የሚደረግበት ቀን ታውቋል፡፡

በስድስት ምድቦች ተከፍሎ ሀምሳ ክለቦችን እንደሚያሳትፍ የሚጠበቀው የ2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ኅዳር 18 መሆኑን ከቀናቶች በፊት በሰራነው ዘገባ የጠቀስን ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ፌዴሬሽኑ ከውድድር እና ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ ሆኖ ከክለቦች ጋር የደንብ ውይይት እና የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የሚደረግበትን ቀን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት ህዳር 9 ቀን 2014 የደንብ ውይይት እና የዕጣ ማውጣት መርሀግብር እንደሚደረግ የተጠቆመ ሲሆን ክለቦች እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ምዝገባ አድርገው ማጠናቀቅ እንዳለባቸውም ፌዴሬሽኑ ጠቁሟል፡፡