ዋልያዎቹ አራተኛ ተጫዋች ከስብስባቸው ውጪ ሆኗል

ዋልያዎቹ በሀዘን ምክንያት ከስብስባቸው አንድ ተጫዋች ውጪ ሲያደርጉ በምትኩም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በትናንትናው ዕለት ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅድሚያ ጥሪ ካቀረበላቸው ተጫዋቾች ውስጥ አራተኛ ተጫዋቹን በድንገተኛ ሀዘን ምክንያት ማጣቱ ታውቋል። በትናንትናው የቡድኑ የልምምድ መርሐ-ግብር ተሳትፎ የነበረው የግብ ዘቡ ፋሲል ገብረሚካኤል ወንድሙ ማረፉን ተከትሎ ከስብስቡ መውጣቱ ተረጋግጧል።

አሠልጣኝ ውበቱ አባተም በፋሲል ምትክ ለቅዱስ ጊዮርጊሱ ባህሩ ነጋሽ ጥሪ አድርገው የነበረ ቢሆንም በፓስፖርት አለመታደስ ምክንያት የአዳማ ከተማው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰውን በአዲስ መልክ በመጥራት ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። ጀማልም ዛሬ ልምምድ መጀመሩ ታውቋል።