ዮሃንስ ሳህሌ በደደቢት በይፋ ተሸኙ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዲሱ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከዛሬ (ሰኞ) ጀምሮ ስራ እንደሚጀምሩ ማስታወቁን ተከትሎ የደደቢት እግርኳስ ክለብ በይፋ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያይቷል፡፡

ዛሬ በደሳለኝ ሆቴል በተካሄደው የስኝት ፕሮግራም ላይ ክለቡ እና አሰልጣኝ ዮሃንስ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሲሆን ደደቢት ለአዲሱ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ የማስታወሻ ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ደደቢትን አመስግነዋል፡፡ ‹‹ ደደቢት የስራ ነፃነትን ስለሰጠኝ ጥሩ ወራት አሳልፌያለው፡፡ አብረውኝ የሰሩ የክለቡ ተጫዋቾች ፣ አመራሮችን እና በዙርያው የሚገኙ ሰዎችን በሙሉ አመሰግናለሁ፡፡ ›› ብለዋል፡፡

የደደቢት ኃላፊዎችም ከዮሃንስ ጋር በነበራቸው ጊዜ ደስተኞች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

‹‹ ለክለባችን ዘመናዊ አሰራርን አምጥቶልናል፡፡ አሰልጣኙ በነበረው ቆይታም ደስተኞች ነን፡፡ በብሄራዊ ቡድኑ መልካሙን እንመኝለታለን ››

አሰልጣኝ ዮሃንስ በወር 75 ሺኅ ብር ደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ከፌዴሬስኑ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰው በይፋ የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝነት መረከባቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *