የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመወዳደሪያ ስታዲየሞች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ውድድሮችን የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በአሁኑ ሰዓት ከተሳታፊ ክለቦች ጋር በመሆን እያወጣ ይገኛል። እጣ ከመውጣቱ በፊትም የሁለቱ ውድድሮች የመወዳደሪያ ስታዲየሞች ይፋ ሆነዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ደግሞ በባቱ ከተማ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ስታዲየሞቹ ይፋ ሲሆኑም ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ውድድሮቹን በአንፃራዊነት ሰላማዊ በሆኑ ቦታዎች ላይ ለማድረግ እንደታሰበ አብራርተዋል። ከዚህ ውጪ በሀገራችን ያለው የስታዲየሞች ጥራትም ታሳቢ እንደተደረገ አውስተዋል።