በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ታውቀዋል

የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ሊጎች የእጣ ማውጣት እና የደንብ ውይይት መርሐ-ግብር በአሁኑ ሰዓት በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ሥነ-ስርዓት ላይ የደንብ ውይይት ከመደረጉ በፊት የውድድር ኮሚቴው የሁለተኛ ዲቪዚዮን በሚል የሚደረገው የሁለተኛው የሊግ እርከን ስያሜ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲቀየር ምክረ ሀሳብ አቅርቦ ተሳታፊ ክለቦች ሥያሜውን አፅድቀዋል። ይህንን ተከትሎ ዋናው ሊግ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በሚል ሲቀጥል ሁለተኛው ሊግ ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ በሚል ስያሜ እንዲደረግ ተወስኗል።

ከዚህ ውጪ በሁለቱ ሊጎች የሚሳተፉ ክለቦችም ታውቀዋል። በፕሪምየር ሊጉ ዓምና ሲወዳደሩ ከነበሩት 10 ክለቦች በተጨማሪ ከሁለተኛው ሊግ ያደጉት ባህር ዳር ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስን በማካተት በ13 ክለቦች መካከል ይደረጋል። ከፍተኛ ሊጉ ደግሞ ከክልል ክለቦች ሻምፒዮና ካደጉት ክለቦች በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሲሳተፉ የነበሩት እና ቡድናቸውን በትነው የነበሩት ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡናን በማካተት በአጠቃላይ በ14 ክለቦች መካከል እንደሚደረግ ተብራርቷል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሀዋሳ ከተማ
አዳማ ከተማ
መከላከያ
ድሬዳዋ ከተማ
ጌዴኦ ዲላ
አዲስ አበባ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቦሌ ክ/ከተማ
ባህር ዳር ከተማ

የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች

ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ቂርቆስ ክ/ከተማ
ልደታ ክ/ከተማ
አራዳ ክ/ከተማ
ሱሉልታ ከተማ
ሀምበሪቾ ዱራሜ
ሀላባ ከተማ
አሰላ ከተማ
ፋሲል ከነማ
ለሚ ኩራ ክ/ከተማ
ሰበታ ከተማ
ሲዳማ ቡና