የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የመወዳደርያ ቦታ ለውጥ ተደርጎበታል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ውድድር ከሀዋሳ ወደ ሰበታ ዞሯል፡፡

የ2014 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሦስት ምድቦች ተከፍሎ ይደረጋል፡፡ በቅርቡ በጁፒተር ሆቴል በተደረገ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ድልድሉ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከክፍያ ጋር በተያያዘ ሳይካተቱ ቀርተው የነበሩ ክለቦችም ክፍያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከትላንት በስቲያ ወጥቶላቸው መደልደላቸው ይታወሳል፡፡ ታህሳስ 2 የውድድሩ መጀመርያ ቀን መሆኑም ይታወቃል፡፡

ከውድድሩ ጋር በተያያዘ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል ተብሎ የተነገረው የመጀመሪያው ዙር የምድብ ለ ውድድር ወደ ሰበታ ዞሯል፡፡ የቦታ ለውጥ ሊያስፈልግ የቻለውም በሀዋሳ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ስለሚደረግ በሚል እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡