የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 1-1 አዳማ ከተማ

ምሽት ላይ የተካሄድው የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማ አንድ አቻ በመሆን ነጥብ ከተጋሩ በኃላ አሰልጣኞችን ለሱፐር ስፖርት አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና

የጨዋታው ፉክክር የተሻለ ስለመሆኑ

ፉክክሩ ጠንካራ ነበር። በተመሳሳይ ደረጃ ያለን ይመስለኛል። ሁለተኛም ከጫና ሁለታችንም አልወጣንም። ያ የፈጠረው የተስተካከለ አጋጣሚዎችን በመፍጠሩ ትክክለኛ የኳስ ፍሰት ለተገቢ የማድረስ በኩል በጣም የተዋጣለት የሚባል አልነበረም። እንግዲህ ቅድም የገለፅኩት ነገሮች ናቸው ለዚህ ሁሉ መንሴው። እንግዲህ ቀስ በቀስ እየተስተካከለ ይሄዳል።

በጊዜ ጎል ማስቆጠራቸው ለማፈግፈጋቸው መንስኤ ስለመሆኑ

አይ አይደለም። እንግዲህ ቅድም ያልኩት ነው ጫና የፈጠረው። ከዚህ በፊት የማሸነፍ ዕድል ስላላጋጠመን ለማሸነፍ ከነበረን ጉጉት ነው። በጊዜ ጎል ስታገባ በራሱ የፈጠረው ነገር ነው። እርግጥ ነው አዳማዎች የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር። ከዛ በኋላ ለመቀየር ሙከራ አድርገናል። ግን ውጤቱ በዛው ሊጠናቀቅ ችሏል።

በማጥቃቱ ላይ ማሻሻል ስለሚገባቸው ነገር

አዎ እናስባለን ማጥቃቱ ስራ ላይ የሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ በጣም ችግር አለብን። ጨርሰነው ልንወጣ የምንችለው እድል አጋጥሞን ነበር። እንግዲህ ችግር እንዳለብን ነው የሚያሳየው ጊዜው እና አጋጣሚው ሲፈቅድ የግድ ነው ሰው ያስፈልገናል። እዛ ቦታ ላይ ግልፅ ነው። ከመጀመርያው ልናመጣቸው ያሰብነው ስላልተሳካ በዚህ ምክንያት ያጥቂ ክፍላችን ሳስቷል። አሁን በይገዙ ላይ ብቻ ጥገኛ ሆነናል። ግን ሌሎቹን ለማብቃት ጥረት እናደርጋለን።


አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – አዳማ ከተማ

የቡድኑ እንቅስቃሴ

ጨዋታውን ባሰብኩት ልክ ሄዷል ብዬ አስባለው። የትኩረት ማነስ ቀድሞ ጎል እንዲቆጠርብን ሆነናል። ያደግሞ ሰወራችንን የበለጠ ከፍ እንዲል አድርጎታል። ቢሆንም ግን በመጀመርያው አጋማሽ የተሻለ ቡድን ነበረን ብዬ አስባለው። ሁለተኛው አጋማሽ ተጫዋቾቼ ጫና ውስጥ ሆነው የሚጫወቱ ይመስለኛል። በተከታታይ ጨዋታ ነጥብ አለማግኘታችን አለማሸነፋችን በሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ቀዝቀዝ እንድንል አድርጎናል። አጠቃላይ ግን ጥሩ ቡድን ሜዳ ላይ አለ ብዬ አስባለው። የመጨረሻው የሜዳ ክፍል ላይ አሁንም ደካሞች ነን እርሱ ላይ ማስተካከል ይጠብቅብናል።

ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱ ከጫና ጋር ስለመገናኘቱ

እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ ነው የምንፈልገው። ለማሸነፍ ስትፈልግ ልክ ነው ጫና ውስጥ መግባት ተፈጥሯዊ ነው በእግርኳስ ውስጥ ቢሆንም ከዛ ውስጥ ወጥተን ሦስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅብናል። ሁሉንም ነገር ሜዳ ላይ እያደረግን ነው። ተስፋ አደርጋለው በቅርቡ የምንፈልገውን ነገር እናገኛለን ብዬ አስባለው።