ከፍተኛ ሊግ | ቂርቆስ ክፍለከተማ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም አዲስ አሰልጣኝም ቀጥሯል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር የተደለደለው የመዲናይቱ ክለብ ቂርቆስ ክፍለከተማ ዋና እና ረዳት አሰልጣኝ ሲቀጥር አስራ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በ2014 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ የሆነው የምድብ ለ ተካፋዩ የአዲስ አበባ ከተማው ቂርቆስ ክፍለከተማ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ከፊቱ ላለበት የሊግ ውድድር ቡድኑን በሚገባ አወቅሯል፡፡ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ውስጥ በቂርቆስ እና አካባቢዋ በአሰልጣኝነት የሰራው ዳንኤል ኃይለሚካኤልን በዋና አሰልጣኝነት፣ በንፋስ ላፍቶ ቆይታ የነበረው ታደሰ እንግዳን በረዳት አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን በመቀጠል አስራ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ አስፈርሟል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሁለት ነባሮችን ውልም አድሷል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አማካይ የነበረው ብሩክ አየለ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ በመጫወት የምናውቀው የመስመር አጥቂው ዮሴፍ ዳሙዬ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ቆይታ የነበረው አማካዩ አሥራት ሸገሬን ጨምሮ ፣ ዳግም አራጌ (ግብ ጠባቂ ከአውስኮድ) ፣ ኤፍሬም ሃይሉ (ግብ ጠባቂ ከነገሌ አርሲ) ፣ አድነው ማዜ (ተከላካይ ከሮቤ ከተማ) ፣ ሳምሶን ተፈራ (ተከላካይ (ከአራዳ ክ/ ከተማ) ፣ ኤርሚያስ በለጠ (ተከላካይ ከደሴ ከተማ) ፣ ምንያህል ወንድሙ (ተከላካይ ፌደራል ፓሊስ) ፣ መላኩ ተፈራ (ተከላካይ ከኢኮስኮ) ፣ ሰለሞን ሀብቱ (አማካይ ከደሴ ከተማ) ፣ ናትናኤል ታረቀኝ (አማካይ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ) ፣ ብሩክ ይደነቅ (አማካይ ከኢኮስኮ) ፣ ሙሉዓለም በየነ (አማካይ ከኮልፌ ቀራኒዮ) ፣ አማረ ሰጡ (አማካይ ከየካ ክ/ከተማ) ፣ አቤል አክሊሉ (አጥቂ ከኤሌክትሪክ) ፣ ጅላሉ ሻፊ (አጥቂ ወልዲያ ከተማ) ፣ ሙከረም አለቱ (አጥቂ ሰበታ ከተማ) እና ኤርሚያስ ዳንኤል (አጥቂ ከአውስኮድ) የክለቡ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡

ክለቡ ቢኒያም ወርቁ እና ኤፍሬም ክፍሌ የተባሉ ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙንም ለድረገፃችን በላከው መረጃ ጠቅሷል፡፡