የትግራይ ክልል ክለቦችን የተመለከተው ውይይት ተደርጓል

የትግራይ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ ያሉ ክለቦች ውሳኔያቸውን የሚያሳውቁበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠ።

ላለፉት ዓመታት በተደረገው ጦርነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ከእንቅስቃሴ ርቀው የቆዩት የትግራይ ክለቦች እሁድ 9:00 ከክልሉ ፌደሬሽን ጋር እንደሚወያዩ መግለፃችን ይታወሳል። ረዥም ሰዓት ወሰደ የተባለው ይህ ውይይት በክለቦቹ የደረሰው ውድመት እና ቀጣይ ወደ እንቅስቃሴ የሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ጥልቅ ውይይት እንደተደረገበት ለማወቅ ተችሏል።

\"\"

ሆኖም በክለቦቹ የቀረበው ሪፖርት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ እና የክለቦቹ ቦርድ አሁን ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለ ቀጣይ እርምጃቸው እንዲወስኑ በመጠየቁ ሌላ ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል። በዚህ መሰረትም ክለቦቹ እስከ ግንቦት 24 ድረስ ሪፖርታቸውን አጠቃለው እንድያስረክቡ የቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል። ከሪፖርቱ መቅረብ በኋላም \’በሊግ ውድድሮች ላይ ይቀጥላሉ ወይስ አይቀጥሉም ?\’ የሚለው ይወሰናል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት ዘጠኝ አባላት ያሉት የክልሉን እግርኳስ ቀጣይ እርምጃ የሚያጠና ቴክኒክ ኮሚቴ እንደሚያቋቁም ሰምተናል። ኮሚቴውም በክልሉ እግርኳስ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦችን እና አሰልጣኞችን ያካትታል ተብሏል።

\"\"