​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

ከደቂቃዎች በኋላ የሱዳን አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።

ዋናው የአፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሩ በፊት በስፍራው ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ (12:30) ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል። በጨዋታውም ተከታዮቹ ተጫዋቾች በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ መካተታቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂ 

ፋሲል ገብረ ሚካኤል

ተከላካዮች

ሱሌማን ሀሚድ 
አስቻለው ታመነ 

ያሬድ ባየህ 

ደስታ ዮሐንስ 

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ 
መስኡድ መሐመድ 

ፍፁም አለሙ 

አጥቂዎች

ዳዋ ሆቴሳ 
አማኑኤል ገብረ ሚካኤል 

ጌታነህ ከበደ