የአፍሪካ ዋንጫ ልዩ ዘገባ ከካሜሩን | በያሬድ ባየህ ዙርያ የተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ታውቋል

ኢትዮጵያ እና ኬፕ ቨርድ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሲያከናውኑ በ11ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ የወጣው ያሬድ ባየህ የተላለፈበት የቅጣት ውሳኔ ታውቋል።

በጨዋታው ገና በጊዜ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣው ያሬድ ባየህን አስመልክቶ የውድድሩ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጫዋቹ ከሜዳ የሚርቅበትን የጨዋታ ቁጥር ይፋ እንዲያደርግ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን በሰማቸው መረጃ መሠረት ተከላካዩ አንድ ጨዋታ ብቻ እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህም መሠረት ያሬድ ባየህ ሐሙስ የሚከናወነው የካሜሩኑ ጨዋታ የሚያመልጠው ሲሆን በቀጣይ ዋልያዎቹ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ሲጫወቱ ወደ ሜዳ መግባት እንደሚችል ተረጋግጧል።