የአፍሪካ ዋንጫ ልዩ ዘገባ ከካሜሩን | የአቡበከር ናስር ወቅታዊ ሁኔታ…?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ባደረገው ልምምድ አቡበከር ናስር ምን አጋጠመው?

በምድብ ሀ ሁለተኛ ጨዋታ በካሜሩን ሽንፈት ካስተናገደ በኋላ ዛሬ ልምምዱን ባደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የፊት መስመር አጥቂ በመሆን ትናንት ዘጠና ደቂቃ የተጫወተው አቡበከር ናስር ዛሬ ባጋጠመው መጠነኛ ጉዳት ምክንያት ልምምድ ሳይሰራ ቀርቷል።

የጉዳቱ ሁኔታ ጉልበቱ ላይ መጠነኛ ማበጥ የታየ ሲሆን በህክምና ክፍሉ አማካኝነት ጉልበቱ ላይ በረዶ ሲታሰርለት ተመልክተናል። እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ጉዳቱ ይህን ያህል ያከፋ እንዳልሆነ እና ለሰኞ ጨዋታ እንደሚደርስ ሰምተናል።

በሌላ ዜና ሽመልስ በቀለ እና ግብጠባቂው ፋሲል ገ/ሚካኤል አሁንም ለቡርኪናፋሶ ጨዋታ እንደማይደርሱ ተረጋግጧል።