​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚመለስበት ቀን ታውቋል

በካሜሩን የነበረው ቆይታ ስኬታማ ያልነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ የሚመለስበት ቀን ታውቋል።

በያውንዴ ከተማ ሁለት ጨዋታዎችን በማድረግ ሽንፈት ያስተናገደው እና ወደ ባፉሳም ከተማ በማቅናት ነጥብ በመጋራት ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕቅዱ ያልተሳካለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ወቅት በዱዋላ ከተማ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ወደ አዲስ አበበ የሚኖሩ በረራዎች ውስን መሆናቸውን ተከትሎ የመመለሻው ቀን እርግጥ ያልነበረው ቡድኑ ሐሙስ አልያም ቅዳሜ ይሆናል ተብሎ ተገምቶ ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ የብሔራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች ጨምሮ ሁሉም የልዑካን ቡድን ነገ ከሰዓት ከካሜሩን እንደሚነሱ እና አመሻሽ ላይ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።

በሌላ ዜና የካፍ ካውንስል የቡድኖችን አጠቃላይ የኮቪድ ምርመራ አስመልክቶ ባደረገው ግምገማ ኢትዮጵያ በተሻለ አፈፃፀም ስሟ በመልካም መነሳቱን ሰምተናል።