የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል

የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካው ክለብ የሙከራ ዕድልን አግኝቶ ወደ ስፍራው አምርቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች በመሆን ያጠናቀቀው አቡበከር ናስር ለሙከራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራቱን ክለቡ አስታውቋል፡፡ 

ከደቡብ አፍሪካው ሀያል ክለብ ማሚሎዲ ሰንዳውንስ የሙከራ ጊዜ ቆይታውን ሙሉ ወጪ ተሸፍኖለት ወደ ስፍራው ያመራው አቡበከር ናስር ሰንዳውንስ እና ኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ድርድር መነሻነት ዕድሉ እንደተገኘም ተገልጿል፡፡