ንግድ ባንክ የሁለት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

ረፋድ ላይ ጋናዊ ተጫዋች ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስምምነት ላይ ደርሰው የነበሩትን ሁለት ዜጋ ተጫዋቾችን ዝውውር ቋጭቷል።

በአዳማ ከተማ መቀመጫቸውን በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ከደቂቃዎች በፊት ሁለገቡን ጋናዊ ተጫዋች ካሌብ አማንኩዋን ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዚህ ቀደም ለመፈረም ተስማምተው የነበሩትን ሁለት ተጨማሪ የውጪ ተጫዋቾችን በይፋ መቀላቀላቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሀገሩ ጋና አሻንቲ ኮቶኮ ፣ ዋፋ እና ካሬላ ዩናይትድ ተጫውቶ የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ያሳለፈው አማካዩ ባሲሩ ዑመር እንዲሁም በአጥቂ እና በአማካይ ስፍራ ላይ ቡልን ለቆ በኢትዮጵያ መድን ቆይታን ያደረገው ሲሞን ፒተር በክለባቸው እስከ መስከረም የሚያቆያቸው ውል ቢኖራቸውም የአንድ ወር ውሉን በስምምነት አፍርሰው በይፋ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ መድን ፊርማቸውን አኑረዋል።