ወልቂጤ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

ወልቂጤ ከተማ የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ረዳትን ይፋ አድርጓል።

የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን በመጨረሳቸዎቹ ጨዋታዎች በሊጉ መክረሙን ያረጋገጠው ወልቂጤ ከተማ ለ2016ቱ የሊግ ተሳትፎው አስቀድሞ ሙሉጌታ ምህረትን በዋና አሰልጣኝነት ከቀናት በፊት የሾመ ሲሆን አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙ በፊት አሁን ደግሞ ረዳት አሰልጣኝ በማድረግ አብዱልሀኒ ተሰማን ሾሟል።

ከዚህ ቀደም ወልቂጤ ከተማን በረዳት አሰልጣኝነት እና በ2013 ደግሞ ጥቂት ጨዋታዎች በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ያገለገለው አብዱልሀኒ ዳግም በወልቂጤ ለመስራት ፊርማውን አኑሯል።