መቻል የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ዛሬ ጀምሯል

በአሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመራው መቻል በዛሬው ዕለት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀምሯል።

ከቀናት በፊት አሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን የሾመው መቻል በዝውውር መስኮቱ ዘግየት ብሎ በመግባት አቤል ነጋሽ፣ አስቻለው ታመነ፣ ነስረዲን ኃይሉ እና ናፊያን አልዮንዚን ያስፈረመ ሲሆን የምንተስኖት አዳነ፣ በኃይሉ ግርማ እና ግርማ ዲሳሳን ውልም ማራዘሙን ዘግበን ነበር። አሁን የዝግጅት ክፍላችን በደረሳት መረጃ መሰረት ክለቡ ዛሬ ከሰዓት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መከወን ጀምሯል።

በዚህም የቡድኑ አባላት ትናንት ምሽት ወደ ቢሾፍቱ ያመሩ ሲሆን በዐየር ኃይል ሜዳ ዛሬ ከ9 ሰዓት ጀምሮ መደበኛ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።