​የአሰልጣኞች አስተያየት | አዲስ አበባ ከተማ 1-2 ወላይታ ድቻ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]


ወላይታ ድቻ አዲስ አበባ ከተማን ያሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅን ተከትሎ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ ተከታዩን  ሀሰብ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ደምሰው በፍቃዱ – አዲስ አበባ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው ጥሩ ነበር የሚገባንን ነገር አድርገናል። እንግዲህ ግን አሁን ትንሽ እየተቸገርን ያለነው ዳኝነት ላይ ትንሽ ችግሮች አሉ። እንዴት እንደምናደርግ እንጃ ምክንያቱም የራስህን ችግር ራስህ ቀርፈህ ትመጣለህ ከልጆች ጋርም የሚታየውን ችግር ራስህ ቀርፈህ ትመጣለህ እንዲህ አይነቱን ነገር መከላከል ግን በጣም ከባድ ነው፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ተሻሽሎ ስለ መቅረብ

“መጀመሪያ እኮ ጥሩ ነበርን፡፡ እግርኳስ ስህተት ነውና ስህተትም ሲኖር ነው ጎልም ሊቆጠርብህ የሚችለው። በዚህም ነው ሊቆጠርብን የቻለው። ስለዚህ ይሄንን ስህተት ቀንሰን የተሻለ ተጭነን ለመጫወት ነበር ጥረት ያደረግነው ጎልም ለማስቆጠር ሞክረናል አስቆጥረናልም ሆኖ ግን መጨረሻ ላይ የተፈጠረውን አይታችኋል፡፡

ውጤቱ ተገቢ ስላለመሆኑ ስለ ቀጣይ ጨዋታ ተፅኖ ስለማሳደሩ

“እውነት ነው አይገባንም፡፡ውጤቱ ተፅእኖ አይኖረውም በእርግጥ ገና ረጅም ጉዞ አለን እኛ ይሄ የመጀመሪያችን አደለም፡፡ምክንያቱም ከዚህ በፊት ከሌላ ቡድን ጋር ስንጫወት ስድስት ደቂቃ አልቆ እንደገና በሰባተኛው ደቂቃ ጎል ተቆጥሮብን ውጤታችንን አጥተናል ስለዚህ አሁንም ያ ነገር ነው የተከሰተው ይሄ በእርግጥ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡”

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም – ወላይታ ድቻ

ስለ ጨዋታው

“ጨወታው ተመጣጣኝ ነው ሜዳ ላይ የነበረው ፉክክር ጠንክሮ ቡድን እንደሚመጡ ታውቃለህ እንግዲህ አሁን የዚህ ዙር ወደ መጨረሻ እየተጠጋ ስለሆነ ክለቦች ጠንክረው መምጣት አለባቸው ባለፈው እኛ አሸንፈን እነሱ ደግሞ ተሸንፈው ስለመጡ ተነሳሽነት ጨምረው እንደሚመጡ እናውቅ ነበር፡፡ዞሮ ዞሮ ተመጣጣኝ የሆነ ጨዋታ ነበረ፡፡በውጤት ደረጃ እኛ ወስደንባቸዋል ለእኛ ጣፋጭ ድል ነው፡፡ስለዚህ እግር ኳስ እንዲህ ነው ጨካኝ ነው ለእኛ ደግሞ ጣፋጭ ድል አስገኝቶልናል ጥሩ ነው፡፡እግር ኳስ ውጤት ነው እኛ ውጤት ተኮር ስለነበር ነጥብ ማግኘት አለብን በዛም ሶስተኛ ሆነናል በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ጥንቃቄ እያደረግን እንሄዳለን በቀላሉ ነው የተቆጠረብን እግር ኳስ ነው እኛም በመጨረሻ ሰአት አስቆጥረናል የእግር ኳስ ባህሪ ነው ተወዳጅ ያደረገው ይሄ ነው ብዙ አነጋጋሪ ነገሮች ነበሩት በሁለት ጨዋታዎች ስድስት ነጥብ ማግኘታችን እንደ ቡድን ጥሩ ነው፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ስለመዳከማቸው

“ስትመራ ሁል ጊዜ ከታክቲክ ውጪ ትሆናለህ ምክንያቱም አስጠብቆ ለመውጣት ታስባለህ ተጋጣሚ ደግሞ ነቅሎ ነው የሚመጣብህ በብዛት ይመጡብሀል ተቀይረው የገቡት እነ ኦዶንጎ ቀላል ተጫዋቾች አደሉም አርባ አምስት ደቂቃ ጉልበት ይዞ ነው የመጣው አንድ ለአንድ አብዶ ሰርቶ የመግባት ነገርም ይታይበት ነበርና በዚህም ውጤት ለመቀየር ብዙ ታትሯል እና ዞሮ ዞሮ እግር ኳሶ በስህተት የተሞላ ነው እኛም ተሳስተናል ግን አሸንፈናል፡፡

ስለ ውጤቱ ተገቢነት

“ከገባብን አንፃር እኛ ያገባነውን አይተሀል። በጥቂት ስህተት ነው የገባብን ስለዚህ ካልተጠናቀቀ እስከ ዘጠና ደቂቃ ፊሽካ እስካልተነፋ ድረስ ይሄ እግር ኳስ ነው ፤ ስለዚህ ይገባናል። እግርኳስን ተወዳጅ ያደረገው ይሄ ስለሆነ ይገባናል፡፡”