ድሬዳዋ ከተማ ለዋና አሰልጣኙ ጥሪ አስተላልፏል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ድሬዳዋ ከተማ በዕግድ ካቆያቸው አሰልጣኙ ጋር ሊነጋገር ነው።

አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮስ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ ኮንትራት ለቀጣይ ሁለት ዓመት ድሬደዋ ከተማን ለማሰልጠን በመስማማት ወደ ውድድር እንደገቡ ይታወሳል። ሆኖም ክለቡ እስከ ዘጠነኛው ሳምንት ድረስ በነበራቸው ቆይታ በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ ባለማየቱ ከአንድ ወር በፊት አሰልጣኙን አግዶ ማቆየቱ ይታወሳል።

ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ ባገኘችው መረጃ መሰረት ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ለአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርስ በደብዳቤ ጥሪ ማስተላለፉን አረጋግጣለች። ድሬዳዋ ከአሰልጣኙ ጋር ያለውን ጉዳይ በህግ የማጣራት ሂደቱ እንዳለ መሆኑን ባስታወሰበት ደብዳቤው ስለክለቡ ጊዜያዊ ውሳኔ አስመልክቶ ከአሰልጣኙ ጋር ለመነጋገር እንደሚፈልግ ገልጿል። በዚህም መሰረት የካቲት ሦስት ማለዳ ላይ አሰልጣኙ በክለቡ ፅህፈት ቤት እንዲገኙ አሳስቧል።

አሰልጣኝ ዘማርያም እና በክለቡ መካከል በቀጣይ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልን እናቀርባለን።